
በጠረጴዛ ልማት ማህበር የህፃናት እንክብካቤ እና የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም በመደበኛነት ከሚደገፉ 1,700 ለችግር ተጋላጭ ህጻናት በተጨማሪ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከጎዳና ተነስተው ወደ ቀያቸው ተመልሰው ትምህርታቸውን ለመከታተል ፈቃደኛ የሆኑ ሕጻናትና ወጣቶችን ጨምሮ ለ1,850 ተማሪዎች በ3 ዙር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
በፈቃዳቸው ከጎዳና ተነስተው ወደ ቤተሰባቸው የሚቀላቀሉ የቁሳቁስ ድጋፋቸውን የሚያገኙት ከወላጆች፥ አሳዳጊዎቻቸው ወይም ከቀበሌ ተወካዮች በየወረዳቸው ከሚገኙ የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ሲሆን ከጎዳና ኑሮ ወደ ት/ቤት የተመለሱ ህጻናት ትምህርታቸውን በተገቢው እየተከታተሉ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ከያሉበት ሲደርስ ልማት ማህበሩ እንደየትምህርት ቤቱ ዩኒፎርም ወይም ሌሎች አልባሳት ድጋፍ ለማድረግም ውጥን ይዟል።
በአጠቃላይ ልማት ማህበሩ ለዚሁ ተግባር የዩኒፎርም/ ሌሎች አልባሳትን ወጪ ሳይጨምር 1,000,000.00 ብር ገደማ ወጪ ያደረገ ሲሆን በሚቀጥሉት ሳምንታት በትምህርት ቁሳቁስ ዋጋ መጨመር ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ ሕፃናት ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው አካባቢ ከሚገኙ ቤተክርስቲያናት ጋር በመተባበር ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
በሶዶ ከተማ የጎዳና ተዳዳሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ እጅግ አሳሳቢ እንደመሆኑ ልማት ማህበሩ ከሚያከናውናቸው ሰፊ የዘላቂ ልማት መርሃ ግብሮች በተጨማሪ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም ከቤተክርስቲያናት ጋር በመተባበር መሰል ተግባራትን ማከናወኑን አጠናክሮ ይቀጥላል። እናመሰግናለን! ወላይታ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያንንና ቺልድረን ቢሊቭ፡፡
ሁሉንም የሰው ልጆች እናገለግላለን!