Moyale-Tilo Mada site

ጉባዔው የተካሄደው ሶዶ ከተማ ከሚገኙ በንግዱ ዘርፍ ከተሰማሩ የሕረተሰብ አባላት፥ ምሁራን እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ነው።

ጉባዔው የተጀመረው የልማት ማህበሩ ዋና ዳይሬተር አቶ በረከት ጣሰው የጉባዔውን ዓላማ እና አጠቃላይ የማህበሩን እንቅስቃሴ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ሲሆን ዓላማውም ቤተክርስቲያን ከመደበኛው የወንጌል አገልግሎት በተጨማሪ በሰው ልጆች ሁለንተናዊ እድገት ምዕመናንን አስተባብራ በመንፈሳዊ፥ ቁሳዊ እና በስነ-አዕምሮ ልማት ማህበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት ነው።

ለዚህም፥ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የየራሱን አስተዋተጽዖ እንዲያበረክት ታልሞ የተካሄደ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምክክር ጉባዔ ሲሆን የላቀ የልማት ስራን ለመስራት እንዲቻል የቲርፈንድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዌይን ጆንሰን የካናዳን ልምድና እስከአሁን ድረስ ለማህበሩ በድርጅታቸው በኩል የተደረገውን ድጋፍ ለተሳታፊዎች አካፍለዋል፤ 

በጉባዔው ማህበረሰቡን በማስተባበር፥ አባላትን ስለ ማደራጀት ጠቀሜታ የማህበሩ የሃብት አሰባሰብ ስራ አስኪያጅ አቶ አልታዬ አየለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሃብት በማሰባሰብ ልማት ማህበሩ በቀጣይ አምስት ዓመታት ሊያከናውናቸው ያቀዳቸው ሰፋፊ የልማት ተግባራት በኢንጂነር ምህረቱ ዮሴፍ ቀርበዋል።

በሚሰበሰበው ሃብት ሊከናወኑ ከታቀዱ እና ለጉባዔው ከተገለጹት መካከል ታላቁን ተልዕኮ በብርቱ መደገፍ፥ ለችግር ተጋላጭ ሕጻናትን መደገፍ እና የትምህርት ልማት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች የልማት ማህበሩ አባል በመሆን እና እንደ አቅማቸውና ፍላጎታቸው በእውቀታቸው፥ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው በየዓመቱ ከ10000.00 ብር እስከ 2500.00 ብር የአባልነት መዋጮ በመክፈል የልማት ማህበሩ ውጥን ከግብ እንዲደርስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቃል ገብተው ውይይቱ ተጠናቋል።

ሁሉንም ያለ ልዩነት እናገለግላለን!